ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢድ-አልፈጥር በዓልን በ2ኛው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ከአቅመ ደካሞች ጋር አከበሩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢድ-አልፈጥር በዓልን በ2ኛው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ከአቅመ ደካሞች ጋር አከበሩ

AMN – መጋቢት 21/2017

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ 1ሺ 446ኛውን የኢድ-አልፈጥር በዓልን ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በሚገኘው 2ኛው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ከአቅመ ደካሞች ጋር አከበሩ።

ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሰው ተኮር እሳቤ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከሎችን በሁሉም ክፍለ ከተሞች በማቋቋም አቅመ ደካሞች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖች ምግብ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውሰዋል።

በረመዳን ጾም ወቅት በከተማዋ በሚገኙ 24ቱም የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በመደበኛነት ለአቅመ ደካሞች ምግብ ከማቅረብ ጎን ለጎን ጾመኞችን የማስፈጠር ተግባር ሲከናወን መቆየቱን የገለጹት ከንቲባ አዳነች፣ የኢድ አል ፈጥር በዓልንም በመረዳዳት እና በመደጋገፍ ማሳለፍ ይገባል ብለዋል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የምገባ ማዕከል ከመገንባት ጀምሮ የምገባ ስራውን እየደገፈ የሚገኘውን የኢትዮጵያ አየር መንገድንም አመስግነዋል።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review