ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች ማዕድ አጋሩ

AMN – ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከማዕከል እስከ ወረዳ ከ400 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ እና የኑሮ ጫና ላለባቸው የከተማችን ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተናል ብለዋል።

እንዲህ ያሉ የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና የሚያቀሉ ስራዎችን እንድንሰራ፣ “መስጠት አያጎድልም” ብለው ከጎናችን በመቆም ጉልበት የሆኑንን የከተማችን ባለሀብቶች በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ ሲሉም አመልክተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review