ከንቲባ አዳነች አቤቤ 26ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ስራ አስጀመሩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ 26ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ስራ አስጀመሩ

AMN-ሚያዝያ 12/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ የተገነባውን 26ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ስራ አስጀምረዋል።

በከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀሳብ አመንጪነት በቀን አንድ ጊዜ እንኳን ምግብ ማግኘት የማይችሉ የከተማዋ ነዋሪዎች በቀን አንድ ጊዜ ንጹህ ምግብ እንዲያገኙ ለማድረግ የምገባ ማዕከላት ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ እየተስፋፉ መቆየታቸው ይታወሳል።

በዛሬው እለትም የትንሳኤን በዓል በማስመልከት በከተማዋ 25ኛ እና 26ኛ የምገባ ማዕከላት ተከፍተው ወደ ስራ መግባታቸውንም ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል።

ትንሳኤ ለሰው ልጅ የተሰጠ ፍቅር የሚታይበት እንደመሆኑ መጠን የምገባ ማዕከላትንም ስንከፍትም ለነዋሪዎቻችን ያለንን ፍቅርና አክብሮት ለመግለጽ ነው ብለዋል ከንቲባ አዳነች።

26ኛው የምገባ ማዕከል ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተገነባ ሲሆን የምገባ መርሃ ግብሩም በቀጣይነት በኮሚሽኑ እንደሚሸፈን በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ አስታውቀዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ 25ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የጉራራ ቅርንጫፍ በዛሬው እለት ማስጀመራቸው ይታወሳል፡፡

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review