AMN- መጋቢት 6/2017 ዓ.ም
ዛሬ ማምሻዉን ከአርባምንጭ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ የነበረዉ ህዝብ ማመላለሻ አዉቶቡስ በወላይታ ዞን በዳሞት ወይዴ ወረዳ በዴሣ ከተማ መዉጫ ባጋጠመው ድንገተኛ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል።
አደጋውን ተከትሎ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ፣
“በአደጋው የሞቱት የወንድም እህቶቼን ነፍስ ፈጣሪ በአፀደ ገነት ከደጋጎቹ ጎን እንዲያሳርፍልን እየተመኘሁ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መፅናናትን እመኛለሁ” ሲሉ ገልጸዋል።
በዚህ ልብ ሰባሪ አደጋ ከሟች ወገኖች በተጨማሪ በ27 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶ ህክምና እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።