ከዜጎች ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች በዚህ ሳምንት ይቀርባሉ

You are currently viewing ከዜጎች ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች በዚህ ሳምንት ይቀርባሉ

AMN – መጋቢት 8/2017 ዓ.ም

መጋቢት 1 ቀን 2017 በተለያዩ ዘርፎች ያላችሁን ጥያቄዎች ላኩ በሚል ለቀረበው ግብዣ በተነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ የተሰጠውን ምላሽ በዚህ ሳምንት እንደሚቀርብ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማህበራዊ ትስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት፣ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም “በትምህርት፣ በጤና፣ በኢኮኖሚ ጉዳዮች እና በሌሎች አምራች ዘርፎች ያሏችሁን ጥያቄዎች እና ማብራሪያ የሚሹ ጉዳዮችን ይላኩልን” በማለት ባሳወቅነው መሰረት የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች የሰጡትን ምላሽ እና ማብራሪያ በዚህ ሳምንት እናቀርባለን ብሏል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review