ከየካቲት 14 ጀምሮ ሀገር አቀፍ የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ይሰጣል- የጤና ሚኒስቴር

You are currently viewing ከየካቲት 14 ጀምሮ ሀገር አቀፍ የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ይሰጣል- የጤና ሚኒስቴር

AMN – የካቲት 11/2017 ዓ.ም

ከየካቲት 14 ጀምሮ ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የልጅነት ልምሻ በሽታ (ፖሊዮ) መከላከያ የነጻ ክትባት ዘመቻ እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የልጅነት ልምሻ በሽታ(ፖሊዮ) ከአምስት ዓመት በታች በሆኑ ሕፃናት ላይ ከፍተኛ የስርጭት ምጣኔ ያለው በመሆኑ በየጊዜው ክትባቱ ይሰጣል።

ጤና ሚኒስቴር በፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ዙሪያ ለሚዲያ ባለሙያዎች ዛሬ የግንዛቤ ማስጨባጫ መድረክ አካሂዷል።

በጤና ሚኒስቴር የክትባት ፕሮግራም ባለሙያ አቶ መስፍን ካሳዬ እንዳሉት የፊታችን የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት ሀገር አቀፍ የልጅነት ልምሻ ክትባት ዘመቻ ይካሄዳል።

በክትባቱ በመጀመሪያ ዙር በ10 ክልሎች በማካሄድ ወደ 14 ሚሊየን የሚጠጉ ህፃናትን ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን አብራርተዋል።

የመጀመሪያው ዙር ከተጠናቀቀ ከአንድ ወር በኋላ ደግሞ በቀሪ ክልሎች ሁለተኛው ዙር ክትባት ዘመቻ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ክትባቱ ቤት ለቤት፣ በትምህርት ቤቶች፣ በህፃናት መዋያና በጤና ተቋማት በነፃ የሚሰጥ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።

መገናኛ ብዙሀን የክትባት ዘመቻው በተሳካ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆን ሙያዊ ሀላፊነት እንዲወጡም ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review