ከ149 ሚሊዮን ብር በላይ የታክስ እዳ ያለባቸው ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ ታገዱ

You are currently viewing ከ149 ሚሊዮን ብር በላይ የታክስ እዳ ያለባቸው ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ ታገዱ

AMN – መጋቢት 10/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከ149 ሚሊዮን ብር በላይ የታክስ ዕዳቸውን ያልከፈሉ 8 ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ የእግድ ትዕዛዝ መተላለፉን ገልጿል፡፡

ቢሮው፣ ለከተማዋ ልማት ሊውል የሚገባውን 149 ሚሊዮን 939 ሺህ 566 ብር የግብር ዕዳ ያለባቸው 8 ግብር ከፋዮች፣ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 44 ንዑስ አንቀፅ ከ1-3 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከሀገር እንዳይወጡ ለፌዴራል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዝርዝራቸውን ማስተላለፉን አሳውቋል፡፡

በየካቲት ወር መጨረሻ ከ 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የግብር ዕዳ ያለባቸው 62 ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ የእግድ ትህዛዝ ማስተላለፉን ቢሮው አስታውሶ፣ ከእነዚህ ውስጥ 3ቱ የግብር ግዴታቸውን ለመክፈል ተስማምተውና የጊዜ ስምምነት በመውሰድ ዕዳቸውን መክፈል በመጀመራቸው እግዱ እንዲነሳ ማድረጉንም ገልጿል፡፡

ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱና በታማኝነት በመክፈል ለከተማዋ ሁለንተናዊ እድገት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱም ቢሮው ጥሪውን ማስተላለፉን ከአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review