AMN – ህዳር 2/2017 ዓ.ም
የጉምሩክ ኮሚሽን ከጥቅምት 22 እስከ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 294 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች መያዛቸውን አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 14 ተጠርጣሪ ግለሰቦች እና 7 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡
አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ የምግብ ዘይት፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና የወጭ ሀገር ገንዘቦች ከተያዙት ዕቃዎች መካከል ይገኙበታል፡፡
በተጠቀሰው ጊዜ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ እና ሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ቀዳሚ መሆናቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡