ከ300ሺ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ሊሰርቁ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በሠላም ሠራዊት አባላት እጅ ከፍንጅ ተያዙ

You are currently viewing ከ300ሺ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ሊሰርቁ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በሠላም ሠራዊት አባላት እጅ ከፍንጅ ተያዙ

AMN-የካቲት 23/ 2017 ዓ.ም

ከ300ሺ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ሊሰርቁ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በሠላም ሠራዊት አባላት እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው 40/60 ኮንዶሚኒየም ቴሌ ታወር ሠፈር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የካቲት 22/ 2017 ከለሊቱ በ9 ሰአት አቶ ደጀኔ ረጋሳ በተባሉ ግለሰብ የግል መኖሪያ ቤት ተሰርቆ ሲከማች የነበረ ብዛቱ ከ300 በላይ የሆነ ፌሮ ብረት በሠላም ሠራዊት አባላት እጅ ከፍንጅ መያዙን የወረዳው ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታውቋል ።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር የሠላም ሠራዊት አባላት በወረዳው አስተማማኝ ሠላም በማስፈን ረገድ ትልልቅ ስራዎች እየሰሩ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተለያየ ጊዜና ቦታ ከጦር መሳሪያ ጀምሮ የተለያዩ ንብርቶችን ከተጠርጣሪዎች በመያዝ ትልቅ ጀብዱ እየፈፀሙ ናቸው ተብሏል።

የወረዳው ሠላምና ፀጥታ ኃላፊ ኢ/ር ሁሴን ሂኒካ በቦታው ተገኝተው የሠላም ሠራዊቱን ማበረታታቸውን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ መረጃ ያሳያል።

ከፖሊስ ጋር በመሆን ተጠርጣሪ ዎችን ለፍርድ ለማቅረብ በፖሊስ በኩል የወንጀል ምርመራ ስራዎች መጀመራቸው ተመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review