ከ375 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

You are currently viewing ከ375 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

AMN-መጋቢት 13/2017 ዓ.ም

ከመጋቢት 4 እስከ መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 321.1 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 54.4 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 375 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል የተለያ ማእድናት ፣አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች ፣ መድኃኒት፣ የቁም እንስሳት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ሞያሌ፣ አዋሽ እና ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በቅደም ተከተላቸውም 92 ሚሊዮን፣ 91 ሚሊዮን እና 52 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ መቻላቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያሳያል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ እና በበረራ የተያዙ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 12 ተጠርጣሪ ግለሰቦች እና ሰባት ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review