ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ደረሰ

You are currently viewing ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ደረሰ

AMN-ጥር 18 /2017 ዓ.ም

4 ሚሊየን 292 ሺህ 600 ኩንታል አፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

ለ2017/18 የምርት ዘመን ከውጭ የሚያስመጣው የአፈር ማዳበሪያ እንደቀጠለ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡

ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ ውስጥ 3 ሚሊየን 45 ሺህ 252 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት ለአርሶ አደሮች እየተከፋፈለ ነው ብሏል፡፡

እንዲሁም ከጥር 24 እስከ የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት በአምስት መርከቦች 2 ሚሊየን 775 ሺህ ኩንታል ተጨማሪ ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ እንደሚደርስ እንደሚጠበቅ ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review