AMN – ታኀሣሥ 22/2017 ዓ.ም
“አሰባሳቢ ገዥ ትርክት ለበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የስነ-ፅሁፍ ምሽት ተካሂዷል።
በስነ ፅሁፍ ምሽቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ፣ ኪነ-ጥበብ የተዛቡ ትርክቶችን ለማቃናት እምቅ አቅምና ጉልበት አለው ሲሉ ተናግረዋል።
ኪነ-ጥበብ ጉልበት፣ ሀብት እውቀትና ክህሎት በመሆኑ ይህንን ጥበብ ለተተኪ ትውልድ ማሻገር እንደሚገባም ተናግረዋል።
በከተማዋ እየተገነቡ የሚገኙ የልማት ስራዎች የኪነጥበብ ስራዎችን ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው ለመዝናኛና ለኪነጥበብ ምሸት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ በበኩላቸው፣ “ሀገራችን ብልጽግናዋን ለማረጋገጥ ያስመዘገበችውን ስኬት በማሰብ የጥበብን ጉልበት በመጠቀም የተዛቡ የትናንት ትርክቶችን እንጠግናለን” ብለዋል።
በስነ-ጽሁፍ ምሽቱ ላይ የተለያዩ ይዘቶች ያላቸው ግጥሞች ባህላዊ ጭፈራዎች፣ እንዲሁም ሙዚቃዎች በአማተር የኪነጥበብ ቡድኖች አባላት ለታዳሚያኑ ቀርበዋል፡፡
በመሀመድኑር አሊ