ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከተወጣጡ የጥበቡ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ኪነ-ጥበብ የአንድ ህብረተሰብ የእድገትና የስልጣኔ ምጥቀት መመልከቻ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኪነ ጥበብ መዝናኛ ብቻም ሳይሆን ግብ እና ተልዕኮ ያለው መሆን አለበት ሲሉም በውይይቱ አብራርተዋል።
በመርሐ-ግብሩም ከውይይቱ ተሳታፊዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በሰጡት ምላሽና ማብራሪያም፣ በአደጉ ሀገራት ኪነጥበብ፣ ኢንዱስትሪ እና መንግስት ተቀናጅተው በመስራታቸው ወደ ብልፅግና መዳረሳቸውን አንስተዋል።
ለዚህም ኪነ ጥበብ ወሳኝ የሚሆነው ከያንያኑ የጥብ ካባን አክብረው መላበስ ሲችሉ ብቻ ነው ብለዋል።
የኪነጥበብ ባለሙያዎች ቁጭት ብቻ ሳይሆን ተስፋን በሚያሳዩና ሀገራዊ መግባባትን በሚፈጥሩ ስራዎች ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ የጥበብ ስራ ጎልቶ በአፍሪካና በዓለም መድረክ የሚታይ መሆን እንዲችል፣ በርካታ የባህልና ታሪክ መሠረት ላላት ኢትዮጵያ ሰፊ እድል የሚፈጥሩ ፀጋዎቿ ማሳያ መሆን እንደሚችሉም አንስተዋል።
ለኢትዮጵያ ብልፅግናም ሆነ ለመጪው ትውልድ ስኬታማነት በጋራ ልንሰራ ይገባል ሲሉም ለዘርፉ ባለሙያዎች ጥሪ አቅርበዋል።
በሚካኤል ህሩይ