ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የደቡብ ሱዳን የፕሬዚደንታዊ የትብብር ሜዳል ተበረከተላቸው

AMN ህዳር 17/2017 ዓ .ም

የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሳልቫኪር ማያርዲት ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፕሬዚደንታዊ የትብብር ሜዳል አበረከቱ፡፡

የተበረከተላቸው የፕሬዚደንታዊ የትብብር ሜዳል ኮሚሽነር ጀነራል የሁለቱን ሀገራት የፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነት በማጠናከር፣ ድንበር ዘለል ወንጀሎችን በመከላከል እንዲሁም የደቡብ ሱዳን ፖሊስ ሪፎርም ሂደትን በመደገፍ የአገልግሎቱን ከፍተኛ መኮንኖች አቅም ለመገንባት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በሰጡት የትምህርትና ስልጠና እድሎች አስተዋፆ መሆኑን ተገልጿል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱም ላይ የደቡብ ሱዳን የፕሬዚደንታዊ ጉዳዮች ሚኒስትር አምባሳደር ቾል ማውትን ጨምሮ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ነቢል መሀዲ እና የደቡብ ሱዳን ፖሊስ ኢንስፔክተር ጀነራል አተም ማሮል መገኘታቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

#Addisababa

#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review