ኮሚሽኑ ከ20ሺ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረጉን አስታወቀ

You are currently viewing ኮሚሽኑ ከ20ሺ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረጉን አስታወቀ

AMN – ሚያዝያ 07/2017

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ባከናወነው የDDR ትግበራ በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያና በአፋር ክልሎች 20ሺ 253 የቀድሞ ተዋጊዎችን የተሃድሶ ሥልጠና በመስጠት ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በDDR አተገባበር ዙሪያ ከባለድርሻ ተቋማትና ከክልል ተወካዮች ጋር ምክክር አካሂዷል፡፡

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጀነራል ደርቤ መኩሪያው በዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ የተጀመረው የDDR ሥራ ሀገራዊ ተልዕኮን በተቀናጀ መንገድ ለመፈጸም፣ ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባሰብ፣ የባለድርሻ አካላትን ሚና ለመለየትና በትብብር ለመስራት ትልቅ አቅም እንዳለው ገልጸዋል፡፡

የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም ምቹ የስራ እድሎች በመፍጠር፣ የሙያና ክህሎት ስልጠናዎችን በማመቻቸትና ተከታታይነት ያለው ድጋፍ በማድረግ ሁሉም የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

በምክክሩ ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (INSA)፣ የመከላከያ፣ የጤና፣ የሠላም እና የሴቶችና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤቶች እንዲሁም የትግራይ፣ የአማራ፣ የኦሮሚያ እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተወካዮች መሳተፋቸውን ከብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመልክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review