AMN – የካቲት 17/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በፌዴራል ደረጃ በምክክር ሂደቶች እንዲሳተፉ ከለያቸው ባለድርሻ አካላት አጀንዳ ለማሰባሰብ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
በሂደቱም ኮሚሽኑ በፌዴራል (በሀገር አቀፍ) ደረጃ ከሚገኙ ተቋማትና ማህበራት አጀንዳ የሚሰበስብ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን መርሃ-ግብሩም በአዲስ አበባ ከተማ በቅርቡ ይከናወናል ተብሏል፡፡
ኮሚሽኑ ከግንቦት 21/2017 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ወራት በ10 ክልሎች እና 2 የከተማ አስተዳደሮች አጀንዳ ሲያሰባስብ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡
በቅርቡ በአዲስ አበባ በሚካሄደው መድረክ በድምሩ 17 ከሚጠጉ የፌዴራል ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎላ አጀንዳዎችን ለመሰብሰብ መታቀዱን የኮሚሽኑ መረጃ ያሳያል፡፡
በሂደቱም የሚከተሉት ባለድርሻ አካላት ጥሪ እየተደረገላቸው ሲሆን ተቋማቱ በወኪሎቻቸው አማካኝነት በሂደቱ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡