
AMN ግንቦት 13/2017
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስራ አመራር አባላት መልማይ ኮሚቴ ለቦርዱ የሥራ አመራር አባልነት የተመረጡ ስድስት እጩዎችን ይፋ አድርጓል።
የኮሚቴው ሰብሳቢ ቀሲስ ታጋይ ታደለ በሰጡት መግለጫ፥ የስራ አመራር ቦርድ አባላትን ለመምረጥ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ 168 እጩዎች በህዝቡ መጠቆማቸውን ገልጸዋል።
ከቀረቡት 168 ግለሰቦች ውስጥ በመልማይ ኮሚቴው የተቀመጡ መስፈርቱን ያሟሉ ስድስት እጩዎች መመረጣቸውንም ተናግረዋል።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስራ አመራር አባል ለመሆን የተመረጡ ስድስት እጩዎችም፦
1.አቶ ተስፋዬ ንዋይ
2.አቶ ተክሊት ይመስል
3.ወይዘሮ ነሲም አሊ
4.ወይዘሮ ዳሮ ጀማል
5.ወይዘሮ ፍሬህወይት ግርማ
6.ያሬድ ኃይለማሪያም(ዶ/ር) ናቸው ብለዋል።