ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ

You are currently viewing ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ

AMN – መጋቢት 1/2017 ዓ.ም

የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር ተወያይተዋል።

ዋና ፀሀፊው በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላፉት መልዕክት፣ አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀመንበር ሆነው ላሳዩት ጽኑ አመራር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዋና ፀሀፊው አክለውም፣ በጠንካራ ወዳጅነት፤ የቀጣናውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ በቅርበት ሰርተናል ብለዋል፡፡

በአዲሱ የስልጣን ዘመናቸው ስኬታማ የስራ ጊዜ እንዲያሳልፉ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) ተመኝተዋል።

ኢጋድ እና የአፍሪካ ህብረት በቀጣናው እና በአፍሪካ ሰላምን፣ ደህንነትና ብልፅግናን ለማስፈን የጀመሩትን የጋራ ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሙሉ እምነታቸው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review