AMN-መጋቢት 10/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በዛሬው እለትም በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት 5,910,000/ አምስት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ አስር ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 2,100,000 ብር፤በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 910,000 ብር ፤ በኮልፌ ክፍለ ከተማ 690,000 ብር፤በየካ ክ/ከተማ 600,000 ብር ቅጣት ቀጥቷል።

በተመሳሳይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር ፤በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር እና በልደታ ክ/ከተማ 400,000 ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ መደረጉን የባለስልጣን መስርያ ቤቱ መረጃ ያመላክታል።
በአጠቃላይ በዛሬው እለት 17 ድርጅት እና 8 ግለሰቦች በድምሩ 5,910,000/ አምስት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ አስር ሺህ/ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻን በመበከል ከድርጊታቸው ያልተቆጠቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።