AMN – መጋቢት 11/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በዛሬው እለትም በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት በድምሩ 4,289,000/ አራት ሚሊየን ሁለት መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 1,315,000 ብር፤ በአቃቂ ክ/ከተማ 800,000 ብር ፤በየካ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር፤በቦሌ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ 500,000 ብር ቅጣት ተቀጥተዋል።
በተመሳሳይ በጉለሌ ክፍለ ከተማ 254,000 ብር ፤በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ
170,000 ብር እና በኮልፌ ክፍለ ከተማ 50,000 ብር ቅጣት በመቅጣት ለመንግስት ገቢ መደረጉን የባለስልጣኑ መረጃ ያሳያል፡፡
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአጠቃላይ 14 ድርጅቶች እና 22 ግለሰቦች በድምሩ 4,289,000/ አራት ሚሊየን ሁለት መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ሺህ/ብር ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ እንዳይበከሉ ለድርጅቶችና ለግለሰቦች በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራቱ የገለጸ ሲሆን ህግ የማስከበሩ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።