ወጣቶች በጎ ተግባራት ላይ በመሣተፍ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ተባለ

You are currently viewing ወጣቶች በጎ ተግባራት ላይ በመሣተፍ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ተባለ

AMN-ግንቦት 21/2017 ዓ.ም

“ደሜን በመለገስ የወገኔን ህይወት እታደጋለው” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስአበባ ከተማ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የተሳተፉበት የደም ልገሳ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሠ አባተ፤ ወጣቶች በዚህ በጎ ተግባር ላይ በመሣተፍ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን መወጣታቸውን አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡

ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ወጣቶች በመርሐ ግብሩ ላይ የተሣተፉ ሲሆን ደም በመለገሥ የወገኖቻቸውን ህይወት መታደግ መቻላቸው ትልቅ የመንፈስ እርካታ እንደሚሠጣቸው ገልፀዋል፡፡ መሰል በጎ ተግባራት ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ ስለሆነ መጠናከር አለባቸውም ብለዋል።

በፀጋ ታደለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review