ዓለም ከ2024 እስከ 2025 ለተጨማሪ አንድ ወር ከፍተኛ ሙቀት ማስተናገዷን ጥናት አመላከተ

You are currently viewing ዓለም ከ2024 እስከ 2025 ለተጨማሪ አንድ ወር ከፍተኛ ሙቀት ማስተናገዷን ጥናት አመላከተ

AMN – ግንቦት 22/2017 ዓ.ም

ግማሹ የአለም ህዝብ በሰው ሰራሽ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ባለፈው አመት ለተጨማሪ አንድ ወር በከፍተኛ ሙቀት አሳልፏል ሲል አዲስ ጥናት አመላክቷል።

የአለም የአየር ሁኔታ ባህሪ፣ ማእከላዊ የአየር ንብረት እና የቀይ መስቀል ቀይ ጨረቃ የአየር ንብረት ማዕከል ተመራማሪዎች ያካሄዱት ይህ ጥናት የአለም ሙቀት መጨመር በጤና ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት በተለይም እነዚህ ተፅዕኖዎች ችላ በሚባሉባቸው በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ላይ ከፍተኛ እንደሚሆን አመላክቷል።

ተመራማሪዎቹ እ.ኤ.አ ከግንቦት 2024 እስከ ግንቦት 2025 በነበሩት ጊዜያት 49 በመቶው የአለም ህዝብ ወይም ወደ አራት ቢሊየን የሚጠጉ ሰዎች ከተለመደው ጊዜ ቢያንስ 30 ተጨማሪ ቀናት ከፍተኛ ሙቀት እንዳጋጠማቸው ማረጋገጣቸውን አር ቲ ኢ አስነብቧል።

ጥናቱ በተጠቀሰው ዓመት ውስጥ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ 67 ከባድ የሙቀት ክስተቶችን ለይቷል።

ይህ ክስተት በተለይም በካሪቢያን አሩባ ደሴት ላይ ተፅዕኖ በማሳደር በስፍራው ከሚጠበቀው በላይ 45 ተጨማሪ የሙቀት ቀናት ታይቷል።

ሪፖርቱ የከፍተኛ ሙቀት ተፅእኖዎችን ለመቅረፍ የተሻለ የሙቀት መቆጣጠር ትግበራ እቅዶች፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶች እና የተሻሻለ የግንባታ ዲዛይን እንደሚያስፈልግ አመላክቷል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review