ዕውቁ የአፍሪካ የሥነ-ጽሑፍ ሰው ንጉጊ ዋቲዮንጎ በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
እስር፣ ግዞት እና ህመም ያላንበረከካቸው ኬንያዊው ጉምቱ ደራሲ ፤ የአፍሪካዊ ዘመናዊ ሥነ-ጽሑፍ ምልክት ተደርገው ይቆጠሩ ነበር፡፡
ደራሲው ስድስት አስርት ዓመታት በተሻገረው የሥነ-ጽሑፍ ጉዟቸው ፤ በዋነኛነት ሀገራቸው ኬንያ ከቅኝ ግዛት እስከ ዴሞክራሲዊ ሥርዓት የነበራትን ጉዞ በመሰነድ ይታወቃሉ፡፡
ንጉጊ ዋቲዮንጎ ለበርካታ ጊዜያት የኖቤል ሽልማት የአሸናፊነት ቅድሚያ ግምት ተሰጥቷቸው ሳይሳካላቸው መቅረቱ አድናቂዎቻቸውን ሲያሳዝን ቆይቷል፡፡
ደራሲው ከምስጉን ጸሐፊነታቸው ባሻገር የአፍሪካዊያን የአፍ መፍቻ ቋንቋዎችሥነ-ጽሑፍ እንዲጎለብት ከፍተኛ ድጋፍ በማድረጋቸው ይታወሳሉ፡፡
ንጉጊ ዋቲዮንጎ እ.አ.አ በ1938 በወቅቱ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት በነበረችው ኬንያ ውስጥ ነበር የተወለዱት፡፡