AMN- ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም
ዘላቂ ሠላምን ማስፈን አማራጭ ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ ነው ሲሉ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናን እንዲሁም የግሉ ዘርፍ እንቅስቃሴዎች እና የሐገር ልማትን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ለጋዜጠኞች እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በመርሐግብሩ ላይ “ሠላም ለልማት” በሚል ርዕስ ፅሑፍ ያቀረቡት የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር) ለአገራት ኢኮኖሚያዊ እድገት ሠላም ተኪ የሌለው መሆኑን የገለፁ ሲሆን የሠላምን መሰረታዊያን መገንዘብ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

ሠላም በማሕበረሰቦች መካከል መተማመንን የሚያሳድግ መሆኑን ያነሱት ዶክተር ዮናስ መተማመንን መገንባት የቻለ ማህበረሰብ ለጋራ ተጠቃሚነት እና በጋራ መስራት የሚችል መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
በሐገር እድገት ውስጥ የግሉ ዘርፍ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን መገናኛ ብዙኃን ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ ቀርቧል፡፡
በአብዱሠላም አንሳር