ባለፉት 5 ቀናት በአፍሪካ ህብረት ሲደረግ የቆየው 20ኛው የዓለም የስራ ድርጅት አካባቢያዊ ጉባኤ ተጠናቋል።
ጉባኤው፣ ፍሬያማ ውይይቶችን በማድረግ እና የውሳኔ ሀሳቦችን በማመላከት ተጠናቋል።
ከ2 ዓመታት በኋላ በ2027 የሚካሄደውን 21ኛውን የድርጅቱን አካባቢያዊ ጉባኤ ለማሰናዳት አምስት ሀገራት ተወዳድረዋል።
ዛምቢያ ከኬኒያ፣ ከቱኒዚያ፣ ከላይቤሪያ እና ከማዳጋስካር ጋር በመወዳደር የአስተናጋጅነቱን ዕድል አግኝታለች።
በአሰግድ ኪዳነማሪያም