የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል የመጠቀም ምጣኔ ከ0 በመቶ ወደ 65 ነጥብ 85 በመቶ እመርታ አሳይቷል- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት

You are currently viewing የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል የመጠቀም ምጣኔ ከ0 በመቶ ወደ 65 ነጥብ 85 በመቶ እመርታ አሳይቷል- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት

AMN – ጥር 21/2017 ዓ.ም

ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ የሲሚንቶ ኢንደስትሪ ለኃይል ግብዓት ፍላጎቱ ከውጭ ሀገራት በሚገባ የድንጋይ ከሰል ምርት ላይ ተመርኩዞ መቆየቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ይሁንና ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል ለመጠቀም በመንግሥት በተደረገ ድጋፍ ትርጉም ያለው ለውጥ መገኘቱ ተገልጿል።

በዚህ የተነሳ ከውጭ በሚገባ የድንጋይ ከሰል ላይ የነበረው የ100 በመቶ ተፅዕኖ ወደ 34 ነጥብ 15 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተመላክቷል። የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል የመጠቀም ምጣኔም ከ0 በመቶ ወደ 65 ነጥበ 85 በመቶ እመርታ ማሳየቱን ከጽህፈት ቤቱ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

ይኽ ለውጥ ከውጭ ከሚገቡ ይልቅ የሀገር ውስጥ ኃብት ቅድሚያ ሰጥቶ የመጠቀም ፖሊሲን ውጤታማነት የሚያሳይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የኃይል ምንጭ ማረጋገጥ እና በውጭ ኃብት ላይ መመርኮዝንም ይቀንሳል ነው የተባለው።

በዚህ ለውጥ አንዱ ቁልፍ ባለሚና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በዳውሮ ዞን በተርጫ አካባቢ ክሌሌ ላይ ያለው ኢቲ ሚኒራልስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ፋብሪካ መሆኑም ተገልጿል። ይህ ፋብሪካ በሰዓት 150 ቶን በማምረት እያደገ ለመጣው ፍላጎት ለሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል ምርት ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት ተመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review