የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ ስማርት ሲቲን የመፍጠር ግባችንን ለማሳካት የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ተካትተውበት የተገነባ ነው ፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ ስማርት ሲቲን የመፍጠር ግባችንን ለማሳካት የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ተካትተውበት የተገነባ ነው ፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ጥር 8/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ዛሬ ባለ 13 ወለል የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ ግንባታን አጠናቅቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ብለዋል::

ዘመኑን የሚመጥን የስራ አካባቢ ለመፍጠር በተለያዩ አካባቢዎች ተበታትነዉ ሲሰጡ የነበሩትን አገልግሎቶች ወደ አንድ ማእከል በማሰባሰብ አገልግሎት የሚሳልጥ መሆኑንም አመልክተዋል

ህንፃው ለአካል ጉዳተኞችም ምቹ፣ለአገልጋይ እና ለተገልጋይ የስራ ቦታን ለመፍጠር እንግልት የሚቀንስ፣ ስማርት ሲቲን የመፍጠር ግባችንን ለማሳካት የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ተካትተውበት የተገነባ ነውም ብለዋል

ይህ ሕንፃ ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት በጥራት ገንብተን ያጠናቀቅነው ይህ ህንፃ በውስጡ 120 ቢሮዎችን ጨምሮ እያንዳንዳቸው 1500 እና 500 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ሁለት የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ በቂ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ጂምናዚየም፣ የሕፃናት ማቆያና መጫወቻ ቦታ እና መሰል መገልገያዎች ተሟልተዉለታልም ብለዋል።

በተጨማሪ ዉጪን በመቆጠብ ከዚህ በፊት ለቢሮ ኪራይ የምናውለውን ሀብት በማስቀረት ለልማት እንድናውል ያስችለናል ነው ያሉት ከንቲባዋ በመልእክታቸው::

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review