የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ላይ ነገ ይወያያል

You are currently viewing የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ላይ ነገ ይወያያል

AMN – ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም

6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ጉባዔ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሄደው መደበኛ ጉባዔው፤ የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ላይ የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የሚያፀድቅ ይሆናል።

በተጨማሪም የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በህግና ፍትህና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review