የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 15ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል

AMN – ጥር 5/2017 ዓ.ም

6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባዔ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ በነገ ጉባዔው የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሁለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ ያቀረበውን የስንብት ውሳኔ አስመልክቶ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የሚያፀድቅ ይሆናል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመትን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review