AMN – ጥር 19/2017 ዓ.ም
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡
ምክር ቤቱ እያካደ ባለው ልዩ ስብሰባው የግብርና ሚኒስቴርን የ2017 በጀት አመት የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማዳመጥ ላይ ነው፡፡
ምክር ቤቱ 2 የብድር ስምምነቶችን መርምሮ ያፀድቃል።
የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እንዲሁም የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።