የሕገ-መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎችን በመመርመር ዜጎች ወቅታዊ ምላሽ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ተናግረዋል፡፡
አፈ-ጉባዔው መሰል ጥያቄዎች በህገ መንግስት ትርጉምና የውሳኔ አፈፃፀም ክትትል ቋሚ ኮሚቴ በሚገባ ታይተው ለምክር ቤቱ ለውሳኔ እንደሚቀርቡ አስታውሰዋል፡፡
ምክር ቤቱ የሕጎችን ሕገ መንግሥታዊነትን ማረጋገጥ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የዜጎች መብት እንዲከበር እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በተመረጡ የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች ላይ ከዘርፉ ምሁራን እና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡