የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የህብረት ስራ ኮሚሽን ፣ የመምህራንን የመኖርያ ቤት ጥያቄ በአጭር ጊዜ መመለስ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት አድርገዋል።
የመምህራንን የመኖርያ ቤት ጥያቄ በፈጠነ ጊዜ ምላሽ ለመስጠት ሲባል ስምምነቱ እንደተደረገ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡
በማህበር የተደራጁ መምህራን ሂደቱን በተከተለ መልኩ የቤት ጥያቄያቸዉን ለመመለስ ፣ያልተደራጁ መምህራንንም የማደራጀቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።
የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ካደራጃቸው 264 የመምህራን ማህበር ውስጥ 96 ማህበራት 25 በመቶው የቅድመ ክፍያ ቁጠባ ያጠናቀቁ በመሆናቸው ቀጥታ ወደ ትግበራ እንደሚገቡ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ልዕልቲ ግደይ አስታውቀዋል።
በትባረክ ኢሳያስ