የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 4ኛ ዙሩ ማጠቃለያ የመሬት ሊዝ ጨረታ ተከፈተ

You are currently viewing የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 4ኛ ዙሩ ማጠቃለያ የመሬት ሊዝ ጨረታ ተከፈተ

AMN- ህዳር 11/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 4ኛ ዙሩ ማጠቃለያ የመሬት ሊዝ ጨረታ ተከፈተ

ቢሮው የ4ኛውን የመሬት ሊዝ ጨረታ ዛሬን ጨምሮ ከህዳር 6፣ 9፣10 ጀምሮ የከፈተ ሲሆን ዛሬ የማጠቃለያውን የመሬት ሊዝ ጨረታ ሰነድ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በተሰናዱ 76 ቦታዎች ከፍቷል።

በቢሮው የለማ መሬት ማስተላለፍ ክትትል ዳይሬክተር አቶ ጫሊ አብርሃም በጨረታው ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውጪ በሁሉም(10) ክፍለ ከተሞች 285 ፕሎቶችን ማዘጋጀቱን ገልፀዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም በ4ኛ ዙር ለጨረታ ከተሰናዱ 285 ፕሎቶች 60 ፕሎቶች ከ3ኛው ዙር ጨረታ የተላለፉ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

የጨረታ ሂደቱ ከብልሹ አሰራር የፀዳና ተአማኒ እንዲሆን በቴክኖሎጂ የታገዘ መሆኑን ገልፀዋል።

ሂደቱንም ተጫራቾችና ወኪሎቻቸው በግልጽ እየተከታተሉት ጨረታው መከፈቱንም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

በሄለን ጀንብሬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review