የመስክ ምልከታው ብዙ የተማርንበትና በጋራ የሚፈቱ ጉድለቶችን የለየንብት ነው – አቶ አህመድ ሽዴ

AMN – ታህሳስ 7/2017 ዓም

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ለመስክ ምልከታ ሲንቀሳቀሱ የሰነበቱት የገንዘብ ሚንስትር አቶ አህመድ ሽዴ የመስክ ምልከታው ብዙ የተማርንበትና በጋራ ሊፈቱ የሚገባቸውን ጉደለቶች የለየንበት ነው ብለዋል፡፡

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጉብሬ ክፍለ ከተማ የግብርና ወተት መንደር ስር የሚገኘውን ኤቢኤም የከተማ ግብርና ማህበር እያመረተ ለከተማው ነዋሪ እያቀረበ ያለውን የወተት ልማት በስፍራው ተገኝተው የተመለከቱት አቶ አህመድ ሽዴ ማህበሩ ይበልጥ መስፋፋት መቻል አለበት ብለዋል፡፡

ሌላው በመስክ ምልከታው የተካተተው በአካባቢው በስፋት የሚመረተውን ቦቆሎና ስንዴ በመጠቀምና እሴት በመጨመር በ240 ሚሊየን ብር የተመሰረተው ግሎባል ዱቄት ማምረቻ ኮምፕሌክስ የስራ እንቅስቃሴ ሲሆን ድርጅቱ ለ 128 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉንና ማህበራዊ ግዴታውን ለመወጠት እያደረገ ያለው ጥረት ላይ የመስክ ምልከታው ተደርጓል፡፡

ሚንስትሩ በመጨረሻ የመስክ ምልከታ ያደረጉት በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኘውን የወልቂጤ አጠቃላይ ሆስፒታል ፕሮጀክት ሲሆን፤ ሚንስትሩ ግንባታው በተያዘለት ጊዜ እንዳልተጠናቀቀና በቀጣይ የክልሉ መንግስት ፕሮጀክቱ በፍጥነት የሚጠናቀቅበትን መንገድ እንዲፈጥርና ለሆስፒታሉ የሚያስፈለጉ የህክምና መሳሪያዎችን ለማሟላትም ከሚመለከታቸው አካላት በጋራ እንሰራለን ማለታቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review