“የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በህዝብ የሚነሱ ቅሬታዎችን የሚፈታ ነው” – አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

You are currently viewing “የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በህዝብ የሚነሱ ቅሬታዎችን የሚፈታ ነው” – አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

ሚያዝያ 20/2017

የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በህዝብ የሚነሱ ቅሬታዎችን የሚፈታ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ፣ ምክትል አፈ-ጉባኤ፣ የምክር ቤቱ አማካሪና አስተባባሪ ኮሚቴ እንዲሁም የጽህፈት ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመገኘት የተቋሙን የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

በጉብኝቱም ለምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ስለ ማዕከሉ አገልግሎት አሰጣጥ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

በገለፃው በማዕከሉ በ12 ተቋማት 41 የሚደርሱ አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ተብራርቷል።

የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በአንድ ማዕከሉ በቅብብሎሽና በቅንጅት አገልግልት የሚሰጡ የተለያዩ ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ይህን መሰል ለሀገር ትልቅ አስተዋፅኦ የሚሰጥ ተቋምን በመገንባት ረገድ የበኩላቸው ጥረት ያደረጉ አካላት ሊመሰገኑ እንደሚገባ እና ተቋማቱን በመደገፍና በማጠናከሩ ረገድም ሁሉም አካል የበኩሉን ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል።

ምክር ቤቱም ማዕከሉን በህግ ማዕቀፍ፣ በክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም በህዝብ ውክልና ስራው አካቶ በመስራት እንደሚደግፍም ማስገንዘባቸውን ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review