የመንገድ ልማት ስራዎችን በኮሪደር ልማቱ ተሞክሮ በፍጥነትና በጥራት ማከናወን እንደሚገባ የምክር ቤት አባላት አሳሰቡ

You are currently viewing የመንገድ ልማት ስራዎችን በኮሪደር ልማቱ ተሞክሮ በፍጥነትና በጥራት ማከናወን እንደሚገባ የምክር ቤት አባላት አሳሰቡ

AMN- ሚያዝያ 22/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ በሚገኘው በዚህ ጉባኤው የምክር ቤቱ አባላት ከህዝብ የሰበሰቡትን የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎችን አቀርበዋል፡፡

መሰረተልማትን በተመለከተ የምክር ቤት አባላት ባነሱት ጥያቄ የመንገድ ልማት ስራዎችን በኮሪደር ልማቱ ተሞክሮ በፍጥነት እና በጥራት ማከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የውሀ ስርጭት በስታንዳርድ እንዲሆን እየተሰራ ቢሆንም ፍትሀዊ ስርጭት እንዲኖር አሁንም ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል፡፡

ከመብራት ጋር ተያይዞ ያረጁ እና ሊወድቁ የደረሱ ፖሎች በነዋሪዎች ዘንድ ስጋት መደቀናቸውን ያነሱት የምክር ቤት አባላት ይህንን ስጋት ለመቅረፍ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የሰብል ምርቶች ላይ የታየው የዋጋ መረጋጋት የሚያስመሰግን ነው ያሉት የምክር ቤት አባለት የፋብሪካ ምርቶች እና ሸቀጣሸቀጦች ዋጋን በዘላቂነት መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ አንስተዋል፡፡

የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በተቋቋሙ የህብረት ስራ ማህበራት ላይ በትኩረት እየተሰራ ቢሆንም በለጠፉት ዋጋ በማይሸጡ ማህበራት ላይ ተጠያቂነትን ማስፈን ይገባል ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review