የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት ማድረስ እንዲችሉ እተሰራ ነው- ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

You are currently viewing የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት ማድረስ እንዲችሉ እተሰራ ነው- ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

AMN- ሚያዝያ 06/ 2017

የመንግስት ትምህርት ቤቶችን በማብቃት ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች ሁሉ ለማድረስ እየተሰራ ይገኛል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል፣ የመምህራንን አቅም በማሳደግና በሌሎችም የአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ዘርፎች የተጀመሩ ሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቅሰዋል።

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 700 ትምህርት ቤቶችን ለማብቃት ትምህርት ሚኒስቴር እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው፣ በትምህርት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት እጅግ ትልቁ ተግባር መሆኑን ጠቁመው፣ ከዚህ አንጻር እየተሰራ ያለው ስራ ተስፋ ሰጭ መሆኑን መናገራቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review