የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የስራ ኃላፊዎች በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የስራ ምልከታ እያደረጉ ነው

You are currently viewing የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የስራ ኃላፊዎች በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የስራ ምልከታ እያደረጉ ነው

AMN- ሰኔ 10/2017

በመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ የተመራ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ቡድን በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የስራ ምልከታ እያደረገ ነው።

የኤ ኤም ኤን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋን ጨምሮ የሚዲያው የስራ ኃላፊዎች የተቋሙን የለውጥ ጉዞ ለሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ቡድኑ አብራርተዋል።

ኤ ኤም ኤን በመዲናዋ የተከናወኑ አበይት ክስተቶችን ከጠያቂ መሰናዶዎችና ዘጋቢ ፊልሞች ጋር አዋህዶ ሚዛኑን በጠበቀ የጋዜጠኝነት ሙያ በተለያዩ ቋንቋዎች በመላው ዓለም ተደራሽ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የስራ ምልከታው መንግስት ሚዲያውን ለመደገፍና በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስተካከል የሚያከናውናቸው የለውጥ ስራዎች አካል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ተናግረዋል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የአዲስ ቲቪ፣ የኤፍኤም 96.3 ራዲዮ እና የአዲስ ልሳን ጋዜጣ እንዲሁም የሁሉም ዲጂታል ሚዲያዎች ባለቤት ነው።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review