የመኖሪያ ግቢ እየገባ የመኪና የጎን መስታወት (ስፖኪዮዎችን) የሰረቀው ተከሳሽ በ9 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

You are currently viewing የመኖሪያ ግቢ እየገባ የመኪና የጎን መስታወት (ስፖኪዮዎችን) የሰረቀው ተከሳሽ በ9 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

AMN- ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም

ጨለማን ተገን በማድረግ የመኖሪያ ግቢ እየገባ ስምንት የመኪና የጎን መስታወት (ስፖኪዮዎችን) የሰረቀው ተከሳሽ በ9 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል እንደገለጹት፣ ተከሳሽ ነብዩ ዮሐንስ የተባለው ግለሰብ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 እና 10 አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ በአጥር በመዝለል እና በበር ሾልኮ በመግባት ከሦስት መኖሪያ ግቢ የአራት ተሽከርካሪዎችን ስፖኪዮዎች ስርቆት ወንጀል መፈጸሙን ተናግረዋል።

ተከሳሹ ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ ከአንድ መኖሪያ ግቢ ከተሽከርካሪ ላይ ሁለት ስፖኪዮዎችን ሰርቆ ለመሰወር ሲሞክር በስራ ላይ በነበሩ የወንጀል መከላከል የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር እንደዋለ ገልጸዋል።

ፖሊስ ተከሳሽን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ምርመራ የማስፋት ስራ በማከናወንም፣ ከሌላ ሁለት የመኖሪያ ግቢዎች ከሦስት ተሽከርካሪዎች ስድስት ስፖኪዮዎች መስረቁን ለማወቅ መቻሉንም ጠቁመዋል።

ተከሳሽ በአጠቃላይ 8 ስፖኪዮዎችን እንደሰረቀ የምርመራ መዝገቡ እንደሚያስረዳ ነው ያመላከቱት።

በዚህም የተከሳሹን የወንጀል ምርመራ መዝገብ ሲከታተል የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን ያርማል ሌሎች ወንጀል ፈጻሚዎችን ያስጠነቅቃል ሲል በ9 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንደወሰነበት ኮማንደር ማርቆስ ገልጸዋል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review