AMN- ህዳር 11/2017 ዓ.ም
የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታዋ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያን ጎበኙ
የመከላከያ ሚኒስቴር ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሊዊጂ በጉብኝቱ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የቢሮ የመኖሪያ እና የሆስፒታል ጥገና በጥሩ ሁኔታ መጠናቀቁን አድንቀዋል፡፡
ሌሎች በጀት ሚያስፈልጋቸው ስራዎች በመለየት እና በመመደብ የመሠረተ ልማቱ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለሠራዊቱ የተሟላ ግልጋሎት እንዲሠጡ አበክረን እንሠራለን ብለዋል።
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አሰፋ ቸኮል በበኩላቸው የዕዙ ጠቅላይ መምሪያ አሁን ያለበትን ደረጃ እንዲይዝ ሚኒስትር ዲኤታዋ የሚመሩት ቢሮ ትልቁን ድርሻ ይይዛል ብለዋል፡፡
የመከላከያ ልዩ ልዩ መምሪያዎች ዕዙን ለመደገፍ የሚያደርጉትን የዘወትር ትብብርንም አድንቀው በቀጣይም አብረው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
በዕዙ አቅም የታደሡ ቤቶችና ግንባታዎች ችግር ፈች መሆናቸውና ቀሪው ግንባታ በመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ በቅርብ ጊዜ እንደሚታደስም አቅጣጫ መቀመጡን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ የትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።