የመከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅም በላቀ ደረጃ የማስጠበቅ አስተማማኝ ብቃት ላይ ይገኛል – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

You are currently viewing የመከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅም በላቀ ደረጃ የማስጠበቅ አስተማማኝ ብቃት ላይ ይገኛል – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

AMN- ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅም በላቀ ደረጃ የማስጠበቅ አስተማማኝ ብቃት ላይ እንደሚገኝ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚና የሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የወልወል ድህረ-ምረቃ እና የ25ኛ ሰላም ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን አስመርቋል።

በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ ጄኔራል መኮንኖችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ተመራቂዎች ለአመራርነት ብቁ የሚያደርጋቸውን ዕውቀት፣ ክህሎት እና ብቃት ጨብጠዋል።

ተመራቂዎች የመከላከያ ሠራዊቱን የመፈጸም አቅም ወደ ላቀ ደረጃ እንዲያሸጋግሩ ተስፋ የተጣለባቸው መሆኑንም ተናግረዋል።

ሠራዊቱ የኢትዮጵያን የዕድገት ጉዞ በበጎ የማይመለከቱ ታሪካዊ ጠላቶች እና የውስጥ ተላላኪ ኃይሎችን አፍራሽ ተግባር በታላቅ ብቃት እያከሸፈ ይገኛል ብለዋል።

የመከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅም በላቀ ደረጃ የማስጠበቅ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

የዛሬ ተመራቂዎችም የሠራዊቱን የድል አድራጊነት ጉዞ በታላቅ ሀገራዊ ስሜትና ጀግንነት ማስቀጠል እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱ የዕድገት ጉዞ እንዲረጋገጥ ብሎም ሉዓላዊነቷ እንዲከበር በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ተመራቂዎች የዳበረ ወታደራዊ ልምዳቸውንና ያገኙትን ስልጠና በዕውቀትና ክህሎት በማስተሳሰር ለሀገራቸው እንዲሰሩ አሳስበዋል።

የመከላከያ ሰራዊቱ የጠላቶችን እና የቅጥረኞችን ሴራ በማሸነፍ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዕድገት ጉዞ ከግብ እንድታደርስ በሚያስችለው ብቃት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ተመራቂዎች በእውቀት፣ በክህሎትና በአስተሳሰብ ሙሉ የሚያደርጋቸውን የመሪነት ስልጠና መውሰዳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review