የመዲናዋን የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች በተመለከተ ከነዋሪዎች ጥሪ መቀበል የሚያስችል የጥሪ ማዕከል ስራ ጀመረ

You are currently viewing የመዲናዋን የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች በተመለከተ ከነዋሪዎች ጥሪ መቀበል የሚያስችል የጥሪ ማዕከል ስራ ጀመረ

AMN – መጋቢት 4/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጥሪ ማዕከል መጀመሩን አስታውቋል፡፡

የጥሪ ማዕከሉ ፀጥታን የተመለከቱ ጥቆማና ቅሬታ እንዲሁም በማንኛውም የከተማዋ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ እና በቢሮው አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጥቆማና አስተያየት ለመስጠት ያስችላል ተብሏል ።

በተጨማሪም ቢሮው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ፣ ባለፉት አመታት በተከናወኑ ስራዎች በመዲናዋ አስተማማኝ ሰላም ማምጣት መቻሉን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ጠንካራ የጸጥታ አደረጃጀት መፍጠር ተችሏል ብለዋል።

የለሙት ቴክኖሎጂዎች ወንጀሎችን ቀድሞ ለመከላከል የሚረዱ መሆናቸውንም ያከሉት ኃላፊዋ፣ የተገኙ ውጤቶችን ለመጠበቅ እና ለማስቀጠል ቴክኖሎጂዎች አበርክቷቸው የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ይፋ ያደረገው የጥሪ ማዕከል ነጻ የስልክ መስመር 8882 መሆኑ ተመላክቷል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review