በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የሚዲያ እና የኮሙኒኬሺን ባለሙያዎች “የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሀገራዊ መግባባት ካስማ ፤የትውልድ ግንባታ መሠረት ነው” በሚል መሪ ሀሳብ ዉይይት አድርገዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባለፉት የለውጥ አመታት የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ እና የከተማዋን ገፅታ የቀየሩ ለዓለም ሃገራትም የሚታዩ እና ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች መሰራታቸዉን ተናግረዋል ::
በከተማዋ የዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ግዙፍ ፕሮጅክቶች ተገንብተዋል ያሉት ኃላፊዋ፣ ስራዎቹም በዓለም መድረክ ላይ እዉቅና የተገኘባቸዉ እና ለሌሎች ሃገራት ጭምር ተሞክሮ መሆን ችለዋል ብለዋል::
የሚዲያ ባለሙያዎች የተሰሩ ስራዎችን በማስተዋወቅ ታሪካዊ እና የዜግነት ኃላፊነታቸዉን መወጣት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል::
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አዲሱ ሻንቆ በበኩላቸው፣የሚዲያ ባለሙያዎች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ስራ በመስራት ዜጎችን የጋራ የሚያደርጉ እሴቶችን ማጎልበት ይገባል ብለዋል::
በቴዎድሮስ ይሳ