የመዲናዋ የልማት ስራዎች የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አሻራ ያረፈባቸው መሆናቸው ተመላከተ

You are currently viewing የመዲናዋ የልማት ስራዎች የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አሻራ ያረፈባቸው መሆናቸው ተመላከተ
  • Post category:ልማት

AMN – ግንቦት 22/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከሚገኙ የተለያዩ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት የተወጣጡ አሰልጣኞች በከተማዋ የተሰሩና እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር ቆይታ ያደረጉ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች መንግስት እያከናወናቸው የሚገኙ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች በሚዲያ ከምናየው ባለፈ በተጨባጭ ተመልክተናል ብለዋል።

በተከናወኑ የልማት ስራዎች የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አሻራ ያረፈባቸውን ስራዎችን መመልከታቸውን ገልጸው ይህም ልዩ ስሜት የፈጠረላቸው መሆኑንና በቀጣይም በሐገር ግንባታ ስራ አሻራቸውን ለማሳረፍ ይበልጥ መነቃቃት የፈጠረላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

የተከናወኑ ስራዎች የነገ ሐገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት ጉልህ አስተዋጽኦ ያላቸው መሆኑን እና ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ የሚሰሩ የልማት ስራዎችን በአካል ተገኝቶ በመጎብኘት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

በሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review