የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን የድንበር ንግድ የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን የድንበር ንግድ የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው

AMN – የካቲት 24/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን የድንበር ንግድ የጋራ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን በቢሾፍቱ ከተማ እያካሄደ ነው።

በስብሰባው መክፈቻ የንግድ ትስስር እና የወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ውሃብረቢ፣ የሰብሰባው ዓላማ ሁለቱ ሀገራት የተፈራረሙት የድንበር ንግድ ፕሮቶኮል አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ ለመገምገም እና በቀጣይ ስምምነቱን በመተግበር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር እንደሆነ አንስተዋል።

ወ/ሮ ያስሚን አያይዘውም እንደገለፁት ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በፈረንጆቹ የካቲት 2017 የድንበር ንግድ ፕሮቶኮል የተፈራረሙ መሆኑን አውሰተው፣ ስምምነቱ በድንበር አካባቢ ለሚኖሩ ለሁለቱም ህዝቦች መሰረታዊ የሆኑ የንግድ እቃዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ህዝቦችን በኢኮኖሚ እንደሚያስተሳስር እንዲሁም በድንበር አካባቢ ሠላም እና መረጋጋትን በመፍጠር በኩል ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውም አመላክተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ የጋራ ውይይትንና ትብብርን የሚጠይቁ እንዲሁም የድንበር ንግድ ፕሮቶኮል ስምምነቱን ተግባራዊ ማድረግ ግድ የሚሉን እንደ ኮንትሮባንድና ህገ ወጥ ንግድ የመሳሰሉ ችግሮች እየገጠሙን ነው ብለዋል፡፡

ይህ ውይይትም እነዚህን ችግሮች ለመፍታት እና የድንበር ንግድ ፕሮቶኮል ስምምነቱን ተግባራዊነት ለማጠናከር በእጅጉ እንደሚያግዝ አመላክተዋል።

የውይይት መድረኩ የድንበር ንግድ ፕሮቶኮል ስምምነትን በውጤታማነት ለመተግበር ትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር የሚጎለብትበትን ሁኔታ ለሠፍጠር፣ ልምድ ለመለዋወጥ ፣ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማሳደግ በድንበር አካባቢ ላሉ ህዝቦች በህጋዊ መንገድ የአነስተኛና ጥቃቅን ንግድ ተግባራዊ በሚሆንበት ሁኔታ ላይ እንደሚያተኩር አንስተዋል።

የአንዱ ሀገር ጥቅም የሌላኛውም ጥቅም ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ለጋራ ጥቅም በትብብር መስራት እንደሚገባ መግለፃቸውን ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review