AMN-የካቲት 27/2017 ዓ.ም
የመገናኛ ብዙሃንና የኪነጥበብ ባለሙያዎች በመዲናዋ እየለሙ የሚገኙ የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።
በመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስተባባሪነት ባለሙያዎቹ ከእንጦጦ ተነስቶ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ የሚደርሰውን የወንዝ ዳርቻ ልማት ነው የጎበኙት።
የወንዝ ዳርቻ ልማቱ የከተማዋ የኮሪደር ልማት አካል ተደርጎ በስፋት እየለማ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ የቆሻሻ ማሳያ የነበሩ ወንዞቿን ገጽታ በሚቀይር መልኩ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
ጉብኝቱም እነዚህ የልማት ስራዎችን ሂደትና መዳረሻ ባለሙያዎቹ በጥልቀት ግንዛቤ ኖሯቸው የራሳቸውን አበርክቶ እንዲወጡ አላማ ያደረገ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል።
የመገናኛ ብዙሀን እና የኪነጥበብ ባለሙያዎቹ ከወንዝ ዳርቻ ልማት ባሻገር የጫካ ፕሮጀክት የልማት ሂደትንም የሚጎበኙ ይሆናል።
በፍቃዱ መለሰ