የንግድና ቀጣናዊ ትስሰር ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ተጀምሮ የነበረዉን የእቃ ማከማቻ መጋዘን ደረሰኝ ስርአት በዘላቂነት ማሳደግ የሚያስችል ፕሮጀክት ከ ኤ ጂ አር ኤ ( AGRA) ጋር በመተባበር ይፋ አድርጓል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስሰር ሚኒስቴር ያስቀመጣቸውን ግቦች ለማሳካት የኤክስፖርት ምርቶችን በጥራት: በብዛት እና በአይነት እንዲቀርቡ እንዲሁም ለኢንዱስትሪዎች ለሀገር ውስጥ ገበያ ፍላጎትን ማሟላት እንዲቻል የግብይት ሰንሰለቱን ማዘመን ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ዉሀብረቢ ገልፀዋል::
የግብይት ስርዓቱን ማዘመን ከሚያስችሉ አሰራሮች አንዱ የእቃ ማከማቻ ደረሰኝ ስርዓት መሆኑን የጠቀሱት ወ/ሮ ያስሚን የግሉን ዘርፍ ጨምሮ ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ሲተገበር መቆየቱንም ገልጸዋል::
የእቃ ማከማቻ ደረሰኝ ስርዓት በተለይም ከ2014 ጀምሮ በተደረገው ትግበራ ውጤት የታየበት መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
553 ሺ160 ኩንታል እህል በማሲያዢያነት በመጠቀም 2.2 ቢሊዮን ብር ብድር ለ141 አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መደረጉን ሚኒስትር ዴኤታዋ አብራርተዋል::