የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ወደ ወንዝ እንዲገባ ያደረጉ የንግድ ቤቶች 600 ሺህ ብር ተቀጡ

You are currently viewing የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ወደ ወንዝ እንዲገባ ያደረጉ የንግድ ቤቶች 600 ሺህ ብር ተቀጡ

AMN-የካቲት 30/2017 ዓ.ም

የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ከዋና ፍሳሽ መስመር በማገናኘት ወደ ወንዝ እንዲገባ ያደረጉ የንግድ ቤቶችን 600 ሺህ ብር መቅጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ከዋና መስመር ትቦ ጋር ባገናኙ ሁለት የንግድ ቤቶች በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት እያንዳንዳቸው 300,000/ሶስት መቶ ሺህ/ ብር በድምሩ 600,000/ስድስት መቶ ሺህ ብር በመቅጣት ርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ማንኛውም አይነት ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ ከመልቀቅና ደረቅ ቆሻሻ ወንዝ ውስጥ ከመጣል እንዲቆጠብ አሳስቧል።

ድርጊቱን በሚፈፅሙ ግለሰቦችና ተቋማት በደንብ ቁጥር 180/2017 መሠረት ርምጃውንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከተቋሙ ማኅበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የከተማ አስተዳደሩ የአዲስ አበባ ወንዞች ከመጥፎ ሽታ ተላቀው የመዝናኛ ቦታዎች እንዲሆኑ የጀመረውን ስራ ዳር ለማድረስ ደንብ በማስከበር የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም ገልጿል።

ህብረተሰቡም ደንቡን ተላልፎ የሚገኝ አካል ሲመለከት በነፃ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማ እንዲሰጥ መልዕክት አስተላልፏል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review