የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመነጋገርና በመመካከር መፍታት ባህል ሊሆን ይገባል – ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

You are currently viewing የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመነጋገርና በመመካከር መፍታት ባህል ሊሆን ይገባል – ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

AMN – መጋቢት 27/2017

በሀገራችን የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመነጋገርና በመመካከር መፍታት ባህል ሊሆን ይገባል ሲሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ።

በአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት የክልሉ ህዝብ ወኪሎች በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በባህር ዳር ከተማ እየተከናወነ ባለው በዚህ መርሃ ግብር ላይ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያካተቱ ወኪሎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች የማህበረሰብ ወኪሎችም ተገኝተዋል።

በወቅቱም ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ እንደገለፁት፤ በሀገራችን የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመነጋገርና በመመካከር መፍታት ባህል ሊሆን ይገባል።

ለዚህም እንዲረዳ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ በገለልተኝነት እየሰራ ሲሆን ይህም ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና ሁሉንም ወገን አሸናፊ ማድረግ የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።

የሚያጋጥሙ ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት ምክክሩ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

ችግሮችን ተቋቁመው ወደ ምክክሩ የመጡ ወገኖችን አመስግነው በቆይታቸውም ህዝቡን የሚወክሉ አጀንዳዎች በማስያዝ ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም አስገንዝበዋል።

ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት መነጋገርና መመካር ወሳኝ ነው ያሉት ደግሞ የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገብረስላሴ ናቸው።

ተመካካሪዎች ጥያቄዎችን ከማቅረብ ባለፈ መፍትሄም ማመላከት እንዳለባቸው አስገንዝበው በምክክሩ እኔ አልተወከልኩም የሚል ቅሬታ እንዳይኖር ሆኖ መከናወን እንዳለበትም ገልጸዋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም በበኩላቸው፤ በሀገራችን ለተፈጠሩ ችግሮች የመጨረሻው ዘላቂ መፍትሄ መመካከር ነው ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review