የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች የካዛንቺስ ኮሪደር ልማትን ጎበኙ

You are currently viewing የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች የካዛንቺስ ኮሪደር ልማትን ጎበኙ

AMN ግንቦት 14/2017 ዓ.ም

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከተገነቡ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል የካዛንቺስ ኮሪደር ልማትን ጉብኝተዋል::

ባለሙያዎቹ “የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሀገራዊ መግባባት ካስማ ፤የትውልድ ግንባታ መሠረት ነው” በሚል መሪ ሃስብ ነው እየጎበኙ የሚገኙት ::

በመዲናዋ ባለፉት ጥቂት አመታት የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ እና የመዲናዋን ገፅታ የቀየሩ የልማት ስራዎች መሠራታቸዉን የገለፁት የሚዲያ ባለሙያዎቹ ለዚህ ደግሞ የካዛንቺስ የኮሪደር ልማት ማሳያ ነዉ ብለዋል ::

በመዲናዋ የተገነቡ የልማት ስራዎች ለመጭዉ ትዉልድ እንዲሸጋገሩ የበኩላቸዉን ሚና እንደሚወጡ ተናግረዋል

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review